የኖርዲክ ሃገራት ለአርበኞች ግንቦት ሰባት 2.42 ሚሊዮን ብር ለገሱ!!

በትላንትናዉ ለት 04/06/2016 በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ በስካንዲክ ሃገራት የሚኖሩ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ግብረሃይል አስተባባሪነት የአርበኞች ግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲና፣ ለነፃነት በተደረገዉ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት 800 ሺ የኖርዌጅያን ገንዘብ (2.42 ሚሊዮን ብር) ገቢ ተሰበሰበ። በዕለቱ ዝግጅት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኤርትራ ግንባር እንዲሁም ፕሮፌሰር ጌታቸዉ ኃይሌ በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን የግንቦት 7 አመራር የነበረዉና በኢትዮጵያ መንግስት ከየመን ታፍኖ የተወሰደዉ አቶ አንድአርጋቸዉ ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ ባልተጠበቀ ሁኔታ ከቦታዉ መገኘት ታዳሚዉን ከፍተኛ ስሜት ዉስጥ የከተተ ነበረ በተለይም ወ/ሮ ብዙአየሁ በቦታዉ ላይ በመገኘት ያደረጉት ንግግርና ያቀረቡት ግጥም ታዳሚዉን በስሜት የናጠና አብዛኛዉን የእልህ እንባ ያስነባ ነበረ የገቢ ማሰባሰብያዉን ዝግጅት ለመሳተፍ ከስዊድን የመጡ የድርጅቱ አባሎችና ደጋፊዎች ያቀረቡት በዝሙሮችና ጭፈራዎች የታዳሚዉን ቀልብ የሳቡ ነበሩ

በዝግጅቱ መጀመሪያ ወደ መድረክ የተጋበዙት የስዊድን የአርበኞች ግንቦት 7 ሥራ አስፈፃሚ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዘለሌ ሲሆኑ ለዝግጅቱ መሳካት የስዊድን ሥራ አስፍፃሚ አመራር ከኖርዌይ ግብረሃይል ጋር በመተባበር በጥምረት እንደሰሩት ገለፃ ያደረጉ ሲሆን አያይዘዉም በስዊድን ስቶክሆልም ለኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ በተደረገዉ የስነፅሁፍ ዉድድር አሸናፊ በመሆን የሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነዉ ወጣት ሜዳሊያዉን በኤርትራና በኢትዮጵያ ድንበር ለሀገራቸዉ ነፃነት ለሚታገሉ አርበኞች በስጦታነት እንዲረከብለት በአደራ የላከዉን የሜዳሊያ ሽልማት ለፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስረክበዋል። በመቀጠል ወደመድረኩ የተጋበዙት ለፕሮፌሰር ጌታችዉ እስካሁን በኢትዮጵያዉስጥ ያለዉ አፈናና የኢኮኖሚ ዉድቀት ሂደት አደገኛና አስጊ ሁኔታ ዉስጥ መሆኑን በመግለፅ የወያኔን ስርዓት ማስወገድ አማራጭ የሌለዉ መፍትሄ መሆኑና በአሁን ሰዓት አርበኞች ግንቦት 7 እያደረገ ያለዉ ስልታዊ ትግል ትክክለኛ መፍትሄ መሆኑን በመግለፅ ሆሉም ኢትዮጵያዊ ይህንን ሃገርን የማዳን ጥሪ በመቀበል ወደ ትግበራ እንዲያመራ ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል በማያያዝም በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለዉ ሕዝባዊ አንቢተኝነት የወያኔ አስከፊና ቅጥ የለሺ አገዛዝ ዉጤት መሆኑን በመግለፅ በአፀፋዉ ወያኔ አየወሰደ ያለዉን ኢሰብአዊ የኃይል እርምጃ ኮንነዋል የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ እንደሚያካትትም አያይዘዉ ገልፀዋል።
በመቀጠል ወደመድረክ የተጋበዙት በጉጉት ሲጠበቁ የነበሩት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባደረጉት ንግግር በሚያደርጉት የትግል ሂደት ዉስጥ እንደ ፕሮፌሰር ጌታቸዉ አይነት ሰዉ ያለዉን የሞያና የእዉቀት ግብአት መሰረታዊ መሆናቸዉን ገልፀዉ የአርበኞች ግንቦት 7 ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲና፣ ለነፃነት እየተከተለ ያለዉ የትግል ስርዓት የደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች የአፓርታይድ ስርዓትን ለመደምሰስ የሄዱበት መንገድን እንደሚከተል በመግለፅ የአፓርታይድ ሰርዓት አሁን በኢትዮጵያ ካለዉ አገዛዝ ጋር የሚመሳሰልበትን ነጥቦች በመዘረዘር በጥልቀት ለታዳሚዉ አስረድተዋል በመቀጠልም የትግል ስልቱ ከዉጪ ሃገራት በሚደረግለት ተፋሰስ የሚደጎምና በዛ ላይ መሰረት ያደረገ ሳይሆን ከእያንዳንዱ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በሚደርግ ድጋፍ ትግሉ የዉጤት በር ድረስ የሚቀጥል መሆኑንም አበክረዉ ተናግረዋል አያይዘዉም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከአስከፊዉ የወያኔ ስርዓት በቶሎ ለመላቀቅ ከመቸዉም ግዜ በበለጠ መልኩ አብዝቶና አምርሮ እንዲታገል ጥሪአቸዉን አቅርበዋል።
የምግብ እረፍት በመስጠት የተጀመረዉ የጨረታ ዝግጅት ከፍተኛ ፉክክር የተካሄደበት ሲሆን ነዋሪነታቸዉን በኖርዌይ በርገን ከተማ ያደረጉ አርበኞች ከስዊድን የግንባሩ አባላት ጋር ያደረጉት ፉክክር ቀልብን የሳበ ነበረ፤ በመቀጠልም ኢካደፍ(ኢትዮጵያን ከረንት አፌርስ)በኩል ጨረታዉን ለመዉሰድ የተደረገዉ ዉድድር እጅግ በጣም አስደሳች የነበረ ሲሆን ሌላዉ ማህበረሰብም የነበረዉ ተሳትፎ እጅግ የሚያኮራ ነበረ በስተመጨረሻም የአቶ አንድአርጋቸዉ ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ ለጨረታ የቀረበዉን ምስል በ ከፍተኛዉን ገንዘብ በግለሰብ በመክፈል በማሸነፍ ሽልማቱን ለኖርዌይ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ያበረከቱ ሲሆን የኖርዌይ የአርበኞች ግንቦት 7 ተወካይ ስእሉን ለስዊድን ግንቦት 7 አባላት በስጦታነት አስረክበዋል።
በስተመጨርሻም ዝግጅቱ ሰፋ ላለ የዉይይት መድረክ ክፍት በማደረግ በዝግጅቱ ላይ የታደሙት ማህበረሰቦች ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር በአርበኞች ግንቦት 7 ለፍትህ ለዲሞክራሲና ለነፃነት የትግል ስርዓትና ሂደት በዝርዝር በመወያየት ዝግጅቱ ተጠናቋል።

ትህዴን 15 የኢህአዴግ ወታደሮች እንደተቀላቀሉት አስታወቀ

የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) በድረገጹ እንዳስታወቁ በርከት ያሉ የኢህአዴግ ወታደሮች ስርአቱን በመቃወም የትህዴንን ማሰልጠኛ ማዕከል ሰሞኑን ተቀላቀሉ::

ድርጅቱ እንዳስታወቀውና የኢሕአዴግን ጦር ከድተው ከተቀላቀሉት ወታደሮች ውስጥ የተወሰወኑትን ስም ዝርዝር አስታውቋል::
1ኛ ወታደር ጥጋቡ ሞላ የደቡብ ህዝቦች ብሔር የሆነ አሁን በመከላከያ በማእከላዊ እዝ ከ22ተኛ ክፍለ ጦር ከአንደኛ ሬጅመንት ከአንደኛ ሻንበል ከጋንታ ሁለት ቲም አራት የነበረ።

2ኛ ወታደር ሙሉጌታ ሰዩም የአማራ ብሔር የሆነ ከ22ኛ ክፍለ ጦር አራተኛ ሬጅመንት ሻንበል አራት ጋንታ ሶሰት ቲም አራት የነበረ፣

3ኛ ወታደር መለስ ባንቲ የአማራ ብሔር የሆነ ከሰሜን እዝ 20ኛ ክፈለ ጦር ሶሰተኛ ሬጅመንት ሻምበል አንድ የነበረ፣

4ኛ ወታደር ወልደገብርኤል ገብረሚካኤል የትግራይ ብሔር ከሰሜን እዝ 11ኛ ክፍለ ጦር ሶስተኛ ሬጅመንት የነበረ፣

5ኛ ሃምሳ አለቃ አደም ሙሃመድ የአማራ ብሔር የሆነ ከሰሜን እዝ 13ኛ ክፍለ ጦር የነበረ፣

6ኛ ወታደር ኤቢሳ አብደሰላም የአፋር ብሔር ከ25ኛ ክፍለ ጦር ሶሰተኛ ሬጅመንት አንድኛ ሻምበል የነበረ፣

7ኛ ወታደር አስማማው አፃሴ ከደቡብ ብሔረሰቦች ኦሞ ዞን ሚሊ ወረዳ ከንቲባ ቀበሌ የነበረ፣

8ኛ ወታደር አወል ሙሁዲን የአማራ ብሔር ከ25ኛ ከፈለጦር ሰድሰተኛ ሬጅመንት አንደኛ ሻምበል የነበረ፣
9ኛ ወታደር ተመስገን አግደው ከበንሻጉል ጉሙዝ ብሔር ከሰሜን እዝ ከ11ኛ ክፍለ ጦር አራተኛ ሬጅመንት ሶሰኛ ሻምበል አንደኛ ጋንታ አራተኛ ቲም የነበረ፣
10ኛ ወታደር ኢሳያስ አለሊ የአማራ ብሔር ከማዕከላዊ እዝ ከ22ተኛ ክፍለ ጦር አራተኛ ሬጅመንት የመካናይዝድ ምድብተኛ የነበረ፣

11ኛ ወታደር ክፋሎም ገብረመሰቀል የትግራይ ብሔር ከ11ኛ ክፍለ ጦር አራተኛ ሬጅመንት ሶሰኛ ሻምበል አንደኛ ጋንታ ሶሰተኛ ቲም የነበረ፣

12ኛ ወታደር አበበ አሸብር የአማራ ብሔር ከማእከላዊ እዝ 31ኛ ክፍለጦር አራተኛ ሬጅመንት ሰለያ የነበረ፣
13ኛ ወታደር ግርማይ ገብረሰላሴ ከትግራይ ብሔር ከማእከላዊ እዝ ከ31ኛ ክፍለጦር አራተኛ ሬጅመንት ከሁለተኛ ሻምበል አንደኛ ጋንታ አራተኛ ቲም።

14ኛ ወታደር በሽር የሴፍ የሱማሌ ብሔር የሆነ ከማእከላዊ እዝ ከ22ኛ ክፍለጦር ሰምንተኛ ሬጅመንት ሁለተኛ ሻምበል ሁለተኛ ጋንታ የሚገኝ ሆኖ ።እሱም ወደ ትጥቅ ትግል ለመሰለፍ ምክንያት ከሆኑት በጋራ ከሰጡት ሃሳብ። እኛ ወታደሮች የገዢው ሰርአት እድሜ ማራዘሚያ ከምንሆን በዚህ ወቅት አጋጥሞት ያለው የእርስ በርስ ግጭትና ቀወሰ ወደ ከፋ አደጋ ሳይወጣ ጠመንጃ ታጥቀን አገርንና ህዝብን ለማዳን የድርሻችንን ለመወጣት ተሰልፈናል ብለዋል።

አደም ሙሃመድና በሸር የሴፍ በጋራ በሰጡት ሃሳብ ደግሞ “በአሁን ወቅት የአገሪቱ ወታደር ሆነህ ልትኖር አሰቸጋሪ ነው በማለትና ቀጥለውም ሰራዊቱ ለሰላም ማሰከበር የሚላከውና የሚሰጠው ማእርግና ሌሎች ግልፅ የሆነ ልዩነቶች ስለሚያደርጉ አንድነቱ የተበታተነ በአጠቃላይ እምነት ወኔ አድሮበት በሰራዊቱ ሊቆይ የሚፈልግ የለም፣ በተለይ በአሁን ጊዚ በመላ የአገሪቱ አካባቢዎች ባሉት ግጭቶች የተነሳ በመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ጥያቄና እርሰበራሳቸው ባልተማመኑበት ሁኔታ በመድረሱ በየጊዜው ምርጫቸው ከመከላከያ ትተው እየወጡ እንዳለ አስታውቋል::

ትህዴን ተቀላቀሉኝ ባላቸው ወታደሮች ዙሪያ ከኢህ አዴግ በኩል የተሰጠ መግለጫ የለም::

ለየት ያለ ተፈጥሮ ያለው ህፃን ተወለደ!

በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ በቢስቴማ ጤናጣቢያ አንዲት እናት ለየት ያለ አምሳያ ያለው ህፃን መውለዷን የደቡብ ወሎዞን ኮሙኑኬሽን ቢሮ አስታወቀ::
ህፃኑ ከሰው ልጅ አምሳያ ለየት ያለ ሆኖ በመፈጠሩ የጤናጣቢያው የህክምና ባለሙያዎችን ያስደነገጠ ሲሆን ከሰዓታት በሆላም ህይወቱ ማለፉን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል!

https://scontent-arn2-1.xx.fbcdn.net/v/t1.0-9/13173921_10154400528999587_7673094540755581057_n.jpg?oh=b33c6f7abdbcdffc9f0dcfbf04ca8e3c&oe=57DA02F2

”Upp till bevis Sverige!”

”Upp till bevis Sverige!”https://i0.wp.com/www.omvarlden.se/imagevault/publishedmedia/xju58e6n4gn6fndg0r4u/mesfin-negash.jpgSamtidigt som Sverige dubblade biståndet till Etiopien och tog emot landets utrikesminister rapporteras om att över 200 demonstranter dödats från november till mars. Nu måste biståndsminister Lövin svara på hur regeringen ska se till så att Sveriges strategi för mänskliga rättigheter i Etiopien får effekt. Det skriver Mesfin Negash, programchef Östafrika och Afrikas horn på Civil Rights Defenders.

Det har gått 25 år sedan den nuvarande regeringskoalitionen tog makten i Etiopien med löften om demokrati och respekt för mänskliga rättigheter. En kvarts decennium senare väntar det etiopiska folket fortfarande på demokratiska reformer, rättsäkerhet och yttrandefrihet. Hundratals bloggare, journalister, oppositionspolitiker och människorättsförsvarare sitter fängslade på politiska grunder.

Nyligen välkomnades den etiopiska utrikesminstern Tedros Adhanom med öppna armar i Stockholm av bland andra utrikesminster Wallström, näringsminister Damberg och biståndsminister Lövin. I mars meddelade regeringen att biståndet till Etiopen fördubblas under 2016-2020. Etiopen är det mest välbesökta afrikanska landet av svenska statsråd det senaste året. Statsministern besökte Etiopen inte mindre än tre gånger inför beslutet om det höjda biståndsanslaget.

Trots landets tillväxt beräknas cirka 20 miljoner etiopier vara beroende av humanitärt bistånd. Just nu hotar en svältkatastrof över 18 miljoner människor i den värsta torkan i landet på minst 50 år. Samtidigt visar den etiopiska regeringen ingen som helst politisk vilja till förändring, och har inte tagit några avgörande beslut för att ta landet i en positiv riktning.

De få oberoende organisationer som fortfarande kan arbeta i Etiopien lever med ständiga hot om att stängas ner då finansiering för rättighetsarbete stoppas genom en rad olika politiska beslut. Inga organisationer som jobbar med några som helst rättighetsfrågor får ta emot mer än tio procent av sin årliga inkomst från externa finansieringskällor. Det spelar ingen roll om organisationen jobbar med barns rättigheter, funktionsnedsattas rättigheter eller utbildning om deltagande i val. Den etiopiska regeringen har lyckats väl med sin balansgång mellan att fortsatt livnära sig på utländskt bistånd, samtidigt som oberoende organisationer som jobbar för en demokratisk utveckling och mänskliga rättigheter effektivt har stoppats.

Biståndsminister Lövin kommenterade det höjda biståndsanslaget till Etiopien genom att understryka att det finns ett ”enormt behov av att stärka mänskliga rättigheter” i Etiopien. Både internationella och nationella organisationer som försöker stötta en demokratisk utveckling och stärka mänskliga rättigheter i landet håller med. Enligt regeringens strategi för Etiopien ska biståndet för mänskliga rättigheter gå till grupper vid sidan av den etiopiska statsapparaten. Givet verkligheten för det civila samhället i Etiopien och ett stadigt hårdnande klimat för oberoende organisationer så måste biståndsminister Lövin nu svara konkret på hur regeringen ska se till att Sveriges strategi för mänskliga rättigheter i Etiopien ska säkerställas. Även om det blir besvärligt när portarna på utrikesdepartementet öppnas för att ta emot besökare som utrikesminster Tedros Adhanom.

Samtidigt som Sverige dubblade biståndet till Etiopien rapporteras om över 200 dödade demonstranter från november till mars, många av dem ungdomar som med fredliga medel protesterade mot regeringens planer att överta mark i Oromiaregionen. Regeringens markövertagande skulle innebära att jordbrukare tvångsförflyttas. Ingen har ställts till svars för våldet och det har inte tillsatts någon utredning.

För att det höjda biståndet inte ska bli bortkastade resurser så måste tydliga krav ställas på Etiopiens regering. Den ”kontinuerliga dialog med Etiopiens regering” som biståndsminister Lövin hänvisar till har uppenbarligen hittills inte haft någon effekt på situationen för mänskliga rättigheter i landet.

 

Mesfin Negash

አርበኞች ግንቦት 7 በአርባምንጭ 20 የኢህአዴግ ወታደሮችን የገደልኩት እኔ ነኝ አለ

https://i2.wp.com/www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2015/08/Arebegnoch-Ginbot-7-800x452.jpgየአርበኞች ግንቦት 7 እንዳስታወቀው በአርባምንጭ 20 የመንግስት ወታደሮች ለተገደሉበት ጥቃት ሃላፊነቱን እወስዳለሁ አለ::

አርበኞች ግንቦት 7 ባወጣው መግለጫው “በወጣት አርበኞቻችን ጀግንነት፣ ጽናትና የጉሬላ ጦር ታክቲክ ክህሎት ኮርተናል። ያደረጉት ተጋድሎ ወደፊት ለሚጠብቃቸው ከዚህ የከፋ ትንቅንቅ ይበልጥ የሚያዘጋጃቸው ሲሆን የሕይወት ዋጋ የከፈሉት ሰማዕታት ጓዶቻችን ታሪክ ደግሞ ህያው ሆኖ ይኖራል።” ብሏል::
“በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል ውስጥ በአርባ ምንጭ አካባቢ የሚንቀሳቀሰው አንድ ቡድን ከሚያዝያ 29 ቀን እስከ ግንቦት 1 ቀን ባደረገው የመረረ ፍልሚያ ከሃያ በላይ የጠላት ወታደሮችን ገድሎ ከሃምሳ ያላነሱትን ማቁሰሉንና በጦርነቱም ከአርበኞች ግንቦት 7 ወገንም መስዋዕትነት ተከፍሎአል” ያለው አርበኞች ግንቦት 7 “የአርበኞች ግንቦት 7 ደቡብ ግንባር አባላት በተግባር ያስተላለፉት መልዕክት መሮናል፤ ዝም ብለን እንደ በግ እየተጎተትን አንታሰርም፤ የካድሬዎች የደም ጥም ማርኪያዎች አንሆንም፤ በአገራችንና በሕዝባችን ላይ የሚደርሰውን መከራ እያየን ዝም አንልም፤ ለነፃነታችን መሞት ካለብን፣ ገድለን እንሞታለን:: ይህ ከኮስታራ ሀሞት የወጣ ድምጽ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ ወገኖቻችን ድምጽ ሊሆን ይገባል።”

ግንባሩ ከአርባምንጩ ጥቃት በኋላ ባወጣው መግለጫው “ትግሉን በሰሜን ኢትዮጵያና በድንበር አካባቢ ተወስኖ የማይቀር መሆኑን ይህ የመጀመሪያ ምልክት ነው፤ በሌሎች ቦታዎች ተመሳሳይ ተጋድሎዎች የሚጀመሩበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። በመላው ኢትዮጵያ፤ በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምስራቅና ምዕራብ፤ በዳርና በመሀል አገር እንዲሁም በከተሞችና በገጠሮች አርበኞች ግንቦት 7 ለነፃነት የሚደረገውን ፍልሚያ ያቀጣጥላል። ይህ የነፃነት ተጋድሎ አንዳንዴ ቦግ፣ ሌላ ጊዜ ደብዘዝ ይል ይሆናል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት ሳይሆን ግን አይጠፋም።” ሲል መግለጫውን ቋጭቷል::

ኖርዌይ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከሃገሯ ለማስወጣት ከኢትዮጵያዊው ጠ/ሚ/ር ጋር ያደረገችውን ስምምነት በመቃወም ሰልፍ ተካሄደ

https://i2.wp.com/www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2016/05/Norway-Ethiopians.jpg

https://i0.wp.com/www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2016/05/Norway.jpg

ኖርዌይ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በግዳጅ ወደ ሀገራቸው ለመመሰስ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ያደረገችውን ስምምነት የሚቃወም ታላቅ ሰልፍ ተካሄደ::

ኢትዮጵያውያን በስደት ከሚኖሩባቸው የተለያዩ የአውሮፓና ስካንዴኔቪያን ሀገሮች አንዷ የሆነችው ኖርዌይ ስትሆን በኖርዌይ ሃገር ቁጥራቸው አነስተኛ የማይባል ኢትዮጵያውያን የፓለቲካ ስደተኞች ይገኛሉ። እነዚህ ስደተኞች ከሌላው ሀገር ለየት የሚያደርግ ጠንካራ የፓለቲካ አቋም ያላቸው መሆኑም ይታወቃል። ስደተኞቹ በተለያየ ጊዜያት የገዢውን ፓርቲ ብልሹ አስተዳደር የሚያጋልጡ የፓለቲካ ስራዎችን ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወሳል።

ሆኖም ግን የኖርዌይ መንግስት እ.ኤ.አ በ2012 ከቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ ጋር በኖርዌይ የሚኖሩ ጥገኝነት ጠያቂዎችን አስገድዶ ወደ ሃገር ለመመለስ የሚያስችል ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል። ሆኖም ግን ይህ ስምምነት በተለያዩ ምክንያቶች ተግባር ላይ ሳይውል ቀርቷል። ኖርዌይ በድጋሚ አሁን በያዝነው አመት በፌብርዋሪ ወር እንደገና ስደተኞችን አስገድዶ ወደ ሀገር የመመለሱ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ቴዎድሮስ አደሃኖም ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በኖርዌይ የሚገኙ ታላላቅ የዜና አውታሮች ሲዘግቡ ሰንብተዋል።

ይህንኑ ስምምነት አስመልክቶ በኖርዌይ የሚገኘው የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ማህበር ስምምነቱ ትክክል እንዳልሆነ ተቃውሞውን ለመግለፅ በሜይ 10፣ 2016 ታላቅ ሰልፍ አዘጋጅቷል። ይህ የተቃውሞ ሰልፍ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል። ስደተኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተለይ በቅርቡ በሀገራችን በአደባባይ እየተገደሉ ያሉ ወገኖቻችንን የያዙ ምስሎችንና የኖርዌይ ዜግነት ያላቸውና ከደቡብ ሱዳን ታፍነው በኢትዮጵያ እስር ቤት እየማቀቁ ያሉንትና አሁን ለዘጠኝ አመት የተፈረደባቸው የአቶ ኦኬሎ አኳይ ፎቶግራፍ እንዲሁም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ፎቶግራፎች በመያዝ ስለነሱም አያይዞ ለኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ እየታወቀ ሰዎች በየሰከንዱ እየተገደሉ ባለበት ወቅት ሀገሪቱ በብዙ አቅጣጫ የህዝብ አመፅ ባለበትና ገዢው ፓርቲም ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ሰዎችን እየገደለና እያሰረ ባለበት ሁኔታ ስደተኞችን አስገድዶ ለመመሰል ስምምነት ማድረጉ ለምን እንዳስፈለገ፤ እንዲሁም የኖርዌይ መንግስት ለኖርዌጅያን ዜጎች በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች መዘዋወር አደገኛ መሆኑን መግለጫ እየሰጠ ባለበት ሁኔታ የፓለቲካ ስደተኞችን አሳልፎ መስጠት ሰብአዊነት የጎደለውና የስደተኛ መብት ህግን የሚጥስ መሆኑን ኢትዮጵያውያኑ በሰልፉ ላይ ተናግረዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የስደተኞቹን ጉዳይ የሚከታተሉ የግብረ ሃይሉ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አያሌው ይመር ንግግር ያደረጉ ሲሆን ዝግጅቱም በተያዘለት ሰአት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ከኢትዮጵያውያን ጋር ሊወያዩ ነው

የአርበኞች ግንቦት 7 መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአውሮፓ ከድርጅታቸው ጋር ስብሰባ ሊያደርጉ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መግለጫ አስታወቀ:: ከኖርዌይና ስዊዘርላንድ የአርበኞች ግንቦት 7 ደጋፊዎች በደረሰን ፍላየር መሰረት ፕሮፌሰሩ ከጁን አራት ጀምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ተዘዋውረው በትግሉ ሁኔታ ገለጻ ያደርጋሉ::

https://i2.wp.com/www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2016/05/gebi-masebaseb-norway-768x459.jpg

ጁን 4፥ 2016 የሚያካሂደዉን የአርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሰሜን አዉሮፓ አቀፍ ህዝባዊ ውይይትና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በተመለከተ የተሰጠ አጭር ጋዜጣዊ መግለጫ

ሃገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ካለችበት ውስብስብ ችግር ለመታደግ ለሃገሪቱና ህዝቧ ቅን የሚመኝ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ ህወሓትን ለማስወገድ በሚደረገዉ ተግባራዊ ትግል ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መሳተፍ የሚኖርበት ወቅት ላይ እንገኛለን።
ኢትዮጵያ በአጣብቂኝና በመንታ መንገድ ላይ በምትገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ከዳር ሆኖ መታዘብ ዘረኛውን፣ አምባገነኑንና፣ ፋሽስቱን የህወሓት አገዛዝ ከመደገፍ ተለይቶ እንደማይታይ ብዙዎቻችን እንስማማበታለን።
አርበኞች ግንቦት ሰባት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህሊናውና አቅሙ በሚፈቅድለት የትግል ዘርፍ መሰማራት ይችል ዘንድ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ጥሪዉን ካስተላለፈ ሰንበት ብሏል። በዚህም መሠረት የህወሓትን አፈና በጠነከረ ክንድ ለመመከት የቆረጡ አርበኛ ታጋዮችና ከፍተኛ የአመራር ብቃት ያላቸዉን ምሁራን ጨምሮ በረሃ ወርደው የወያኔን አገዛዝ መፋለም ጀምረዋል። በግምባር መሰለፍ ያልቻሉት ደግሞ በገንዘባቸዉና በእዉቀታቸዉ የሚፈለግባቸዉን በማበርከት ላይ ይገኛሉ፣
ትግሉ የሚካሄደዉ ሃገሪቱን ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠረ፣ ብሎም የሃገሪቱን አንጡራ ሃብት፣እንዲሁም በልመናና በብድር የሚገኘዉን መዋእለ ንዋይ በማሟጠጥ ተቃዋሚዎቹን ለማጥፋት በሚንቀሳቀስ የወንበዴ ቡድንና ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ዉጭ ሌላ ምንም አጋር በሌለዉ የነጻነት ታጋይ መካከል ነዉ፣፣
ለነጻነት የሚደረግ ትግል እልህ አስጨራሽና አድካሚ ነዉ፣ ዉድ ዋጋና በገንዘብ የማይተመነዉን ህይወትም ያስከፍላል፣ዉጤቱ ግን ከሁሉም ነገር የበለጠና ዉድ ነዉ፣፣ በመሆኑም ይህ ወሳኝ ሐገርን የማዳን ጥረት ዉጤታማ እስኪሆን ድረስ ነጻነት ናፋቂ የሆን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ያላሳለሰና ሁለገብ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል፣፣
ይህንን መሰረት በማድረግ June 4, 2016 የሰሜን አዉሮፓ ሃገራትን ያማከለ ታላቅ ህዝባዊ ዉይይትና የገቢ ማሰባሰብያ ፕሮግራም በኖርዌ ሃገር ኦስሎ ከተማ ተዘጋጅቷል፣፣
በዚህ ፕሮግራም ላይ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ መሪ ታጋይ አርበኛ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከበረሃ በመንቀሳቀስ በመካከላችን በአካል በመገኘት ስለትግሉ ማብራሪያ ይሰጣሉ።
ፕሮግራሙ የተዘጋጀዉ ከተለያዩ የሰሜን አዉሮፓ ሃገሮች ተዉጣጥቶ በተቋቋመ ግብረ ሃይል ሲሆን በኖርዌ ሃገር በሚገኘዉ የዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት የበላይ አሰተባባሪነት ነዉ፣፣ በዚህ ታላቅ አህጉራዊ ስብሰባ ላይ በኖርዌይና በተለያዩ የሰሜን አዉሮፓ ሃገራት የሚኖሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በብዛት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፣
ፕሮግራሙ ከየትኛዉም የአለማችን ክፍል ለሚመጣ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጅ ክፍት ነዉ፣፣ በተለይም በስካንዲኒቪያንና፣ በአጎራባች የአውሮፓ ሃገራት የምንኖር ነጻነት ናፋቂ ዜጎች የፕሮግራሙ ታዳሚዎች በመሆን የበኩላችንን እንድንወጣ ግብረሃይሉ በትህትና ያሳስባል፣፣
በተለያዩ አህጉራት ያላችሁና በአካል መገኘት የማትችሉ ኢትዮጵያዊያን ለዚህ ሃገር የማዳን ጥሪ የትግል አጋርነታችሁን በሚያመቻችሁ መንገድ ታሳዩ ዘንድ አስተባባሪ ግብረ ሃይሉ በአክብሮት ይጋብዛል።
የፕሮጋራሙ ቀን፣ June 4, 2016
ሰአት፣ ከ14፣00 ሰአት ጀምሮ
የፕሮግራሙ ቦታ፣ በቀጣይ የሚገለጽ ይሆናል
ተጋባዥ እንግዳ፣ የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ መሪ ከኤርትራ

ኢትዮጵያችን በክብር ለዘላለም ትኖራለች!!
የዲሞራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ
ሜይ 13፣ 2016 ኖርዌይ፣ ኦስሎ,