የወያኔ ትልቁን “ኩዴታ”

የወያኔ ትልቁን “ኩዴታ” ጥምረት ውህደትን “በሾኬ የጣለበትን” የወሬ ጋጋታ እንግዲህ አለፍነው። ተመስገን። ሰማይ አልተደረመሰም። የወያኔ ቲቪ ሰዓት እላፊ ሰራ። በዳያስፖራ ያሉ የወያኔ አሽከሮች “የፍየል ወጠጤ” ዓይነት መልክት አስተጋቡ። ወያኔን አትንኩብን አሉ። የአንድን ሰው መክዳትን ድል አድርገው ሊያደናቁሩ ተሟሟቱ። አዲስ የተሻሻለች ህወሃትን የሚሹ ምሁራንም የቆሙበት በግልጥ ታየ። ሌሎችም ጥምረት ውህደቱን ተቹ። ህብረት እንፍጠር ያላችሁ ሳይገባችሁ ነው አሉ። የሞላ መክዳትት ወሬ ጥቂቶችን አናዞ እያለፈ ነው።መጭውን የወያኔ “የረቀቀ ስለላ ውጤት” እስክንሰማ እንጠብቃለን።የሞላ አስከዶም ተገቢው ጎራ መዘነቅ ወሬው ቶሎ ከሰመ::ከዚህ የሚያልፍ አይደለም።ግን መጥኔ ለአዲሳባ!

ፕሮፓጋዳ ጥበብ ነው። ተንኮልም አለበት። ወያኔ ደግሞ በተንኮል እንጂ በጥበብ አይታማም። ፕሮፓጋዳ ዓይን ያወጣ ውሸት ማቅረብ አይደለም። የሚሰራ መሆን አለበት። ፕሮፓጋዳን በስልት ከያዙት ጋር ሲተያይ፡ ወያኔ ዛሬ ገና በድንጋይ ዘመን እየኖረ ነው። የወያኔ ፕሮፓጋዳ በመለስ አገዛዝ ይሻል ነበር።የአስራ አንድ ከመቶው “ዓመት ካመት እድገት”፤”አልሸባብ ሊወረን ነው””በቀን ሶስቴ መብላት”ትዝ የሚሉ ናቸው። ዛሬ በሞላ መክዳት የሆነውን የህወሃት ግርግር መለስን መቃብሩ ውስጥ ሆኖ የሚያወራጨው ነው።የሞላ መክዳት ጊዜ አለመግዛቱን መለስ ቶሎ ይረዳው ነበርና።አንድ የትጥቅ እንቅስቃሴ ብርታቱን የሚያገኘው ወይ በተሰዋ፤ በተሰዋች ጓድ ነው፤ወይ በከዳ፤ በከዳች ጓዲት ድርጊት የአባላት መብገን ነው። ከርእዮትና ከዓላማ ጎን ለጎን እኒህ ያሉት ተጨባጭ ክስተቶች ናቸው ትግልን ወደፊት የሚገፉት።የሞላ አስከዶም መክዳት በጊዜ መሆኑ ከፍ ካለ ጥፋት የሚሰውርና ለደምሂት ሰራዊት ጠብቆ መዋቀሪያ እድል ማስገኘቱ ይታመናል። ታች ከምናየው የፕሮፓጋዳ ሊቅ ከነበረው የአዶል ሂትለር ባለሟል አባባል ብዙ ታዝበን የወያኔንና አሽቃባጮቹን ጅል ድርጊት እንታዘባለን።ህዝባዊ ትግል የተራ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ የሚሆነው በህወሃቶች ጭቅላት ውስጥ ብቻ ነው።ህዝባዊ ትግል በተራ ፕሮፓጋዳ የሚገታ ቢሆን እንዴት ከየካቲት ስልሳ ስድስት አንስተን ከዚህ ደረስን? ፕሮፓጋዳንና ድንፋታ ለደርግ የእለት ተለት ተግባር አልነበረም ?እስቲ ወደ ዮሴፍ ጎብልስ እንሂድ። እሱ እንዲህ ይላል፡

ፕሮፓጋዳ ሰዎችን መሳብ፤ማሳመን እውነት ነው ብየ ለተቀበልኩት፤ ይህ ነው ፕሮፓጋዳ ማለት ። ሲጀመር መግባባት አለ። ይህ መግባባት ፕሮፓጋዳን እንደ መሳሪያ ተጠቅሞ መግባባትን(ስብከትን) ወደ ፖለቲካ ይቀይረዋል።ማቸነፍ ዋናው ነገር ነው።ፕሮፓጋዳ የተራ ሰዎች ምግባር አይደም።የሙያተኞች ነው።ደስ የሚል ወይም በንድፈ ሃሳብ ትክክል መሆን የለበትም። የሚያስደንቁ፤የተዋቡ ንግግሮችን ባደርግ ሴቶችንም እምባም ባስረጭ ግድ አሰጠኝም።የፖለቲካ ንግግር ዓላማው ማሳመን ነው።እኛ ትክክል ነው የምንለውን።ክፍለ ሃገር ሆኘ የምለው በርሊን ሆኘ ከምለው ይለያል።ቤይሩት ሆኘ የምናገረው ፋረስ አዳራሽ ሆኘ ከምለው አይመሳሰልም።ይህ የንድፈ ሃሳብ ሳይሆን የተግባር ጉዳይ ነው። የጥቂት ገልጃጆች ማህበር ሳይሆን ሰፊውን ህዝብ የሚያንቀሳቅስ ነው የምንሻው።ፕሮፓጋዳን ተቀባይነት ሊኖረው ይገባል። አእምሮን ማራኪ መሆን የለበትም።የፕሮፓጋዳ ተግባር ምሁራዊ እውነቶችን መፈተሽ አይደለም።እዲህ ያለው ፍተሻ የራሱ ጊዜና ቦታ አለው።እኔ እዲህ ያለውን እውነት የምፈትሸው ከቢሮዬ ተቀምጨ እንጂ ከስብሰባ አዳራሽ ሆኘ አይደለም።(1)

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s