መንግስት በጎንደር የ17 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን አመነ አንዱን የገደልኩት እኔ ነኝ ብሏል

ትናንትና  በጎንደር በ እስር ቤት ላይ በደረሰ ቃጠሎ የበርካታ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ዘግበን ነበር:: መንግስት አንድ ሰው መግደሉን ሲያምን ሌሎቹ 16 ሰዎች ህይወት የጠፋው በቃጠሎው ወቅት ከ እስር ቤቱ ለማምለጥ ሲጋፉ ነው አለ::

የአማራ ክልል ፖሊስ ለመንግስት ሚድያዎች በሰጠው መግለጫው ትናንት ህዳር 21፣ 2008 በጎንደር ማረሚያ ቤት ከቀኑ 7፡30 አካባቢ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ ከማረሚያ ቤቱ ለመውጣት በተደረገው ግፊያ የ16 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰው ሊያመልጥ ሲል ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ገልጿል::

እንደ አይን እማኞች ገለጻ ከሆነ ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር ከ30 በላይ ቢሆንም መንግስት ቁጥሩን ማሳነሱንና በ እጁ የጠፉትን ቁጥር ወደ አንድ ብቻ ማሳነሱ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል:: እንደ እማኞች ገለጻ አብዛኛው እስረኛ በመንግስት እጅ የተገደለ እንጂ ከ እስር ቤት ከ እሳት ለማምለጥና ለመውጣት ሲጋፉ አይደለም::

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s