የተማሪዎቹ ቁጣ ዛሬም በተለያዩ ከተሞች ቀጥሏል – በአዳማ፣ አምቦ፣ ሱሉልታ፣ ወለጋና ቡሌ ሆራ ውጥረት አለ | በሃሮማያ አንድ ተማሪ ተገደለ

2ኛ ሳምንቱን የያዘው የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ በአዳዲስ ከተሞችም ቀጥሎ መዋሉ ተሰማ:: በአዲስ አበባ እና በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የተገደሉ ተማሪዎችን ለማሰብ ተማሪዎች ተሰብስበው የነበረ መሆኑ ታውቋል:: በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎቹ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሎ በዚያው አካባቢ የነበረ አንድ የ9ኛ ክፍል ተማሪ በፌደራል ፖሊስ መገደሉ ተሰምቷል:: እየተደረገ ያለው ተቃውሞ ከዩኒቨርሲቲዎች ወርዶ እስከ መለስተኛ ሁለተኛ ትምህርት ቤቶች ደርሷል:: በቡራዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎቹ ማስተር ፕላኑን እና የተፈጸመውን ግድያ ሲያወግዙ የዋሉ ሲሆን አሁንም አካባቢው በፌደራል ፖሊስ ተወጥሮ እንደሚገኝ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል:: ይህ የተማሪዎች ተቃውሞ በአዳማ ዩኒቨርሲቲም የተሰማ ሲሆን ፌደራል ፖሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን የሃይል እርምጃዎችን ሲወስድ እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል:: በሱሉልታም እንዲሁ የመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከነዩኒፎርማቸው አደባባይ የዋሉ ሲሆን ማስተር ፕላኑን አጥብቀው ሲያወግዙት ውለዋል:: በአምቦ ዩኒቨርሲት በነበረው ተቃውሞ በርካታ ተማሪዎች በደረሰባቸው ድብደባ ቢጎዱም ይህ የባሰ ውጥረቱን እንዳባባሰው መረጃዎች ጠቁመው ተማሪዎቹ አሁንም አምርረው በመቃውም ላይ መሆናቸው ታውቋል:: በሙገር የተደረገው ተቃውሞ ከተማሪዎች አልፎ ገበሬዎችን እና የመንግስት ሠራተኞችንም ጭምር ያካተተ እንደነበር ሲሰማ ውጥረቱ አሁንም እንዳለ መሆኑ ተሰምቷል:: የአዲስ አበባ አዲሱ ማስተር ፕላን ገበሬዎችን የሚያፈናቅልና በስፍራው የሚኖረውን አርሶ አደር ተጠቃሚ የሚያደርግ ሳይሆን የመሬት ቅሚያ ነው በሚል በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተነሳው ተቃውሞ ማብረጃው ማስተር ፕላኑን መሰረዝ ብቻ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ:: መንግስት ይህን ካላደረገ ወይም ሰብስቦ ካላነጋገረ ይህ ተቃውሞ ወደ ህዝባዊ አመጽ ሊሸጋገር እንደሚችል ይገመታል::

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s