ወያኔ ህዝብ ለሕዝብ የሚያግጫ ስለሆነ እንጠቀቅ ይላሉ ዶር በያን

ዶር በያን የቀድሞ የኦነግ አመራር አባል ነበሩ። አሁን ደግሞ በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ከፍተኛ አመራር አባል ናቸው።ሰሞኑን በኦሮሞ ተማሪዎችና በጎንደር በተነሳው ሰላማዊ ተቃዉሞ ዙሪያ ፣ ለኢሳት በሰጡት ቃለ ምልልስ ሁሉም ካልተባበረ፣ በተናጥል የሚደረግ ዉጤት እንደማያመጣ ገልጸዋል።
“እምቢተኝነት፣ ተቃዉሞ በመላው ኢትዮጵያ መካሄድ አለበት። የኦሮሞ ተማሪዎች ሲያመጹ ሌላው ቁጭ ብሎ ካየ፣ ወይንም በጎንደር ወይም በየአገሪቷ ያለ ማህበረሰብ ሲያምጽ ፣ ኦሮሞው ወይንም ሌላው ቁጭ ብሎ ችግር ነው” ያሊት ዶር በያን አሰቦ፣ በዘር በኃይማኖት ኢትዮጵያውያን ሳይከፋፈሉ በጋራ ለመበት፣ ለዲሞክራሲና ለነጻነት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

“ሕዝቡ ፍትህ ጠምቶታል፤ በአገሩ በሰላም መኖር ጠምቶታል” ያሉት ዶር በያን፣ “ህዝብ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ በአራቱም ማእዘናት ተባብሮ፣ ለሚደረገው የዴሞክራሲና የነጻነት የፍትህ ጥያቄዎች በጋራ መቆም አለበት” ብለዋል።

ወያኔ ላለፉት 24 አመታት ህዝብ ለሕዝብ እያጋጫ፣ ያለፉ ታሪኮች አጣሞ እያቀረበ፣ በተለይም በኦሮሞው እና በሌሎች ኢትዮጵያዊያን መካከል መግባባትና መቀባበል እንዳይኖር ሲያደርግ እንደነበረ ይታወቃል። በአንድ በኩል ፣ ለኦሮሞው ሌሎች በተለይም አማርኛ ተናግሪዎች “ከዚህ በፊት የጨቆኑህ ናቸው፣ የገደሉህ ናቸው፣ ነፍጠኞች ናቸው ..” እያሉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለሌሎች ደግሞ “ኦሮሞው ስልጣን ካገኝ ይጨርሳል፤ እኛ ነን የምንጠብቅህ” በማለት ህዝብን ከሕዝብ በመከፋፈላቸው፣ የተጠናከረ ሁሉን ያቀፈ ትግል ማድረግ አልተቻለም ነበር።

ዶር በያን ይህ አይነቱ ሕዝብብ ከህዝብ የመከፋፈል እኩት ተግባራትን ገዢው ፓርቲ አሁንም ሲስተማቲክ በሆነ የሚቀጥልበት እንደሆነ በመገጽል ትክቅ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
“ሕዝብ ለሕዝብ እያጋጫ ስልጣኑን ለማራዘም እንደሚሞክር መጠበቅ አለበት። ተደርጓል ከዚህ በፊትም። ወደፊትም የሚጠበቅ ነው። ስለዚህ ንቅናቄው (በኦሮሞ ተማሪዎችና በጎንደር የተጀመረው) ፣ ሕዝቡ against the regime ተነስቶ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ተባብሮ የሚቃወምበት መሆን አለበት እንጂ፣ ህዝብ ለሕዝብ እንዳይጋጭ፣ ሕዝቡ ለሕዝብ በምንም አይነት ተቃዉሞ ዉስጥ እንዳይገባ፣ መጠንቀቅ ያስፈልጋል” ሲሉ በአራቱም ማ፤እዘን ለሚኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ አደርገዋል። የሚሊዮኖች ድምጽ

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s