ሰልፈኞች በምዕራብ ሸዋ ግንደበረት የመለስ ዜናዊን ፓርክ በእሳት አነደዱት – አጋርፋና ወሊሶ በተኩስ ድምጽ ተናውጠዋል

እየተካረረ የመጣውና በኦርሚያ ክልል ትናንሽ ከተሞችን ጨምሮ እየተደረገ ያለው ሕዝባዊ ቁጣ በኦሮምያ ክልል በምእራብ ሸዋ ዞን በአቡነ ግንደበረት ደርሶ በዚሁ ከተማ ውስጥ ያለውንና ካለ ሕዝቡ ፍላጎት በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ስም ተሰይሟል ያሉትን ፓርክ አቃጠሉት::

በምእራብ ሸዋ አቡነ ግንደበረት ከተማ የሕዝቡ ቁጣ ገንፍሎ ከወጣ ወዲህ በስፍራው የተሰማራው የአጋዚ ኮማንዶ እንኳ ሊያስቆመው እንዳልቻለ የገለጹት ምንጮች ፓርኩን የሟቹን የቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊን ስም በእርግማን መልክ እያነሱ ሲያቃጥሉት እንደነበር ምንጮች ዘግበዋል::

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በአምቦ አሁንም አለመረጋጋቱ ያለ ሲሆን በወሊሶ ዛሬም በተፈጠረው ግርግር ሰዎች እየሞቱ መሆኑን የደረሰው መረጃ ይጠቁማል:: በወሊሶ ንግድ ቤቶች ሱቆቻቸውን ዘግተዋል:: አካባቢው በተቃውሞ እና በአጋዚ ጦር ጥይት ተናውጣለች::

በአጋርፋም ከፍተኛ ተቃውሞ መነሳቱ ተሰምቷል:: አካባቢው በጥይት ድምጽ እየተናወጠ ነው::

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s