ጀግናዋ ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ አርበኞች ግንቦት7ን መቀላቀሏን በይፋ ገለጸች

ርእዮት አለሙ ለረጅም ጊዜ በወያኔ እስር ቤት እንድትማቅቅ ያበቃት ጉዳይ “በቃ!” የሚል ግድግዳ ላይ የተጻፈ መፈክርን ፎቶ አንስታ ለጋዜጠኞች በመላኳ ነበር። ጉዳዩ ይህ ሆነ ሳለ ወያኔ በካንጋሮ ፍርድ ቤቱ አቁሞ የከሰሳት ግን “በሽብር” ወንጀል ነው፣ የስልክ ትእዛዝ ከህወሓት ሹማምንቶች እየተቀበሉ ፍርድ የሚገመድሉት ዳኞችም ሳያቅማሙ ርእዮት አለሙ ላይ ፈርደው አይጥና ተባይ ወደሚፈነጭበት ማጎሪያቸው ላኳት።Reeyot Alemu joins Patriotic Ginbot7
ጭካኔያቸው በዚህ አላበቃም ርእዮት እስር ቤት ሆና በህመም ስትሰቃይ ተገቢውን ህክምና እንዳታገኝ አደረጉ።
በዚያን የጭለማ ወቅት ነበር ርእዮት አለሙ ወያኔን በሰላማዊ መንገድ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ውጤት ሊያመጣ በሚችል መንገድ ለመታገል የወሰነችው።
ቀደም ሲል ርእዮት እስርቤት በነበረችበት ጌዜ በጻፈችውን ጦማር “… እስካሁን የሄድንበትን መንገድ ልንመረምር ይገባል” የሚለውን መልእቷን አስታውሳ ውሳኔዋን ስታብራራ፣
“… በኔ ግምገማ ወያኔን በሰላማዊ ትግል ብቻ ታግሎ ማሸነፍ አይቻልም… ፖለቲከኛን ማሰር ብቻ ሳይሆን ወያኔዎቹ በፈለጉ ጊዜ የፖለቲካ ፓርቲን ማፍረስ የሚችሉበት ሁኔታ ነው ያለው…”
“ሃገር ቤት ተመልሼ መጻፍ የመቀጠል እቅድ የለኝም… መጨረሻዩ ቃሊቲ መመለስ እንደሆን አውቃለው… በአሁኑ ወቅት አይደለም ጋዜጣ ላይ መጻፍ ፌስቡክ ላይ ሃሳብን መግለጽ እንኳ የሚያሳስር ነገር ሆኗል”
“ስለዚህ ባጭሩ አርበኞች ግንቦት7ን ለመቀላቀል ወስኜ ተቀላቅያለሁ…”
ርእዮት አለሙ እሳት የሚተፋ ብእሯን ይዛ አርበኞቹን ተቀላቅላለች፣ በርካታ የአርበኞች ግንቦት7 አባላት እና ደጋፊዎችም አበጀሽ በማለት ውሳኔዋን በማድነቅ ላይ ናቸው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s