ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ታሰረ

የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ አዘጋጅ ሆኖ በሃገር ቤት መረጃን ለሕዝብ ሲያደርስ የቆየው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ዛሬ በደህንነት ኃይሎች ታፍኖ ተወስዶ መታሰሩ ተሰማ:: ከሃገር ቤት የመጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ሕወሓት የሚመራው መንግስት ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በተነሳው የሕዝብ ቁጣ በመደናገጥ በርካታ አክቲቭስቶችን እያሰረ ይገኛል::

https://i2.wp.com/www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2015/12/gEtacew-shiferaw.jpg

ኦህዴድን ጥርስ ያለው አንበሳ በማስመሰል በየሚዲያው እንዲነገር በማድረግ ሕዝቡን ያደናገረው ሕወሓት የሚመራው መንግስት በተለይ ሰሞኑን በኦሮሚያ የተነሳውን የሕዝብ ቁጣ ለማረጋጋት የኦህዴድ ባለስልናት እንደ አባዱላ ገመዳ ያሉት በየሚዲያው በማቅረብ የመንግስትን ፖሊሲ እንዲተቹ በማድረግና ከሕዝብ ጎን እንደቆሙ በማስመስል ፕሮፓጋንዳቸውን ከሰሩና ሕዝብን የማረጋጋት ሥራ በኋላ ቀስ በቀስ አክቲቭስቶችን ማሰራቸውን ቀጥለዋል::

ትናንት አቶ በቀለ ገርባ የታሰሩ ሲሆን እስካሁን ድረስም ከ3000 በላይ ሰው በዚሁ በኦሮሚያ ከተቀሰቀሰው የሕዝብ ቁጣ ጋር ተያይዞ ታስረዋል::

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው መንግስትን በፌስቡክ እንዲሁም በነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ደባውን ሲያጋልጥ የቆየ ሲሆን በመጨረሻም ከቤቱ ወደ ሥራ ሊሄድ ሲውጣ ደህነነቶች እና ፖሊሶች አፍነው ወስደው ማዕከላዊ አስረውታል::

በሌላ በኩልም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑት ቴዎድሮስ አስፋው ከቤቱ እንዲሁም አቶ ዳንኤል ተስፋዬ ከፍርድ ቤት ታፍነው ተወስደው ታስረዋል::

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s